Fana: At a Speed of Life!

በጅቡቲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 104 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 104 ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው ጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ጋር በመተባበር ነው ዜጎችን በሁለት ዙር ከነጋድ ባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ያደረገው።

ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ በተጀመረው ክትትል ስራ በየቀኑ በርካታ ዜጎችን የህግ ከለላ እንዲያገኙ በማድረግ ከእንግልት እና ከሞት መታደግ መቻሉም ተገልጿል።

ይህ ተግባርም በሚቀጥሉት ጊዜያት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.