Fana: At a Speed of Life!

 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኮሪደር ልማት ስራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በክልሉ በኮሪደር ልማት በሚተገበሩ ስራዎች አፈጻጸም እና የልማት ስራዎች ላይ ከክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

መድረኩ የኮሪደር ልማት ዝግጅት እና አፈጻጸም፣ በሰባቱ የክልል ማዕከላት የቢሮ ግንባታ፣ በከተሞች ተግባራዊ ስለሚደረጉት ሞዴል የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ፣ የከተማ ግብርና አፈጻጸም እና ዝግጅት ላይ እየመከረ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.