Fana: At a Speed of Life!

የፎርድ ኩባንያ ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ሊቀንስ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የመኪና አምራች ኩባንያ የሆነው ፎርድ በእንግሊዝ እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ሊቀንስ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኩባንያው ሰራተኞቹን ለመቀነስ የወሰነው ባጋጠመው ዝቅተኛ የገበያ ትስስር ምክንያት የኤሌክትሪክ መኪኖች በበቂ ሁኔታ አለመሸጣቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ፎርድ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በእንግሊዝ ብቻ ከ800 በላይ ሰራተኞችን እንደሚቀንስ ያስታወቀ ሲሆን፤ በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ባሉት ቅርንጫፎቹ ደግሞ ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞችን እንደሚቀንስ አስታውቋል፡፡

የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች፣ የምርት ልማት፣ ደጋፊ የስራ ዘርፎች እና የኩባንያው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሰራተኞች ሊቀነሱ ከሚችሉ ሰራተኞች ውስጥ መሆናቸው ነው የተገለፀው፡፡

እስከ ፈረንጆቹ 2027 ከሰራተኞቹ ጋር በህጋዊ መንገድ በመስማማት እና ተገቢውን ካሳ በመስጠት ውሉን እንደሚያቋርጥ ኩባንያው ገልጿል፡፡

ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ በመኪና አምራችነት የሚታወቀው ፎርድ ኩባንያ የኢንዱስትሪ ትራንሰፎርሜሽን ለማድረግ የፖሊሲ አውጭዎች፣ የንግድ ማህበራት እና የመንግስት አካላት አብረውት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል መባሉን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.