Fana: At a Speed of Life!

የአፍ ውስጥና የፊት ቀዶ ሕክምና ዘርፍን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍ ውስጥ፣ የመንጋጋና የፊት ቀዶ ሕክምና ዘርፍን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ የአፍ ውስጥ፣ የመንጋጋና የፊት ቀዶ ሕክምና ሐኪሞች ማህበር ኮንፈርንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የአፍ ውስጥ፣ የመንጋጋና የፊት ቀዶ ሕክምና ማህበር ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ተፈራ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ የዘርፉን ሕክምና በተለያዩ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

ሕክምናው የኮቪድ 19 ወረርሽን ተከትሎ ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰው ÷አሁን ላይ በስምንት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ማህበሩ በዘርፉ የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴዔታ አየለ ተሾመ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷የአፍ ውስጥ፣ የመንጋጋና የፊት ቀዶ ሕክምና ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ሀገራት ተሞክሮዎችን በመቅሰም አገልግሎቱን ለማሳደግ በትብብር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በኮንፈረንሱ በዘርፉ በርካታ ልምድ ያካበቱ ከአፍሪካ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ ሐኪሞች መሳተፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.