Fana: At a Speed of Life!

በማንቼስተር ከተማ ኤአይ ካሜራ ለትራፊክ ቁጥጥር አገልግሎት እየዋለ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ማንቼስተር ከተማ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (ኤአይ) ካሜራ ለትራፊክ ቁጥጥር አገልግሎት እየዋለ መሆኑ ተነገረ።

በከተማዋ 3 ሺህ 200 ሹፌሮች በማሽከርከር ላይ ሳሉ ስልክ ሲያወሩ እና ቀበቶ ሳያስሩ ሲንቀሳቀሱ በኤአይ ካሜራዎች ተይዘዋል።

በከተማዋ ባለፉት አምስት ወራት የትራፊክ ቁጥጥሩን ለማጠናከር በሰዎች በሚንቀሳቀስ ካሜራ እና በኤአይ ካሜራ በጋራ ሙከራ ላይ ውሏል፡፡

የሙከራዎቹ ውጤትም በእንግሊዝ በ2040 የመኪና አደጋ እና የመንገድ ላይ ሞትን ዜሮ ለማድረግ ያለመው የመንገድ ደህንነት ፕሮግራም በተከበረበት ሳምንት ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡

በሙከራው መሰረትም በከተማዋ 3 ሺህ 200 ሹፌሮች ሌላ ተሸከርካሪ ከኋላቸው እያለ እና መንገደኞች ፊት ለፊት እያሉ ስልክ ሲያዎሩ በኤአይ ካሜራ ተይዘዋል፡፡

በተጨማሪም ሹፌሮች ከተወሰነ ፍጥነት በላይ ሲያሽከርክሩ እና የአደጋ ቀበቶ ሳያጠልቁ ሲሽከረክሩ በካሜራ ታይተዋል፡

የማንቼስትር ከተማ ምክትል ከንቲባ ኬት ግሪን÷ ሹፌሮች መኪና በሚያሽከረክሩበት ወቅት ስልክ ማውራት እና የደሀንነት ቀበቶ አለመልበስ በከተማዋ ለተከሰቱ በርካታ የትራፊክ አደጋዎች ምክንያት መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በእነዚህ አደጋዎችም በርካታ ሰዎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውንም ነው ምክትል ከንቲባዋ የገለፁት፡፡

በማንቼስተር ከተማ ተግበራዊ የተደረገው የኤአይ ካሜራ ከመስከረም 3 እስከ ጥቅምት 24 ብቻ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ መኪኖችን በእይታቸው ውስጥ አስቀርቷል መባሉን ፍሊት ኒውስ ዘግቧል፡፡

በዚህም ኤአይ ቴክኖሎጂ የትራፊክ እንቅስቃሴን በመቆጣጠር ረገድ ባለው ጠቀሜታ አገልግሎት ላይ መዋሉ ተነግሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.