Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የስንዴ ምርት ስብሰባ ሒደት በትብብርና በፍጥነት እንዲከናወን አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስንዴ ምርት ስብሰባ ሒደት በትብብርና በፍጥነት እንዲከናወን አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥የስንዴ መኸር መጀመሩን ተናግረዋል።

”እናም በዚህ ዓመት ብዙ ምርት ስላለን ይህን ሂደት በሀገር አቀፍ ደረጃ በትብብር ማፋጠን አለብን” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የስንዴ ምርት ስብሰባ ከአጨዳ እስከ ጎተራ የሁሉንም ዜጋ ትግግዝ እንደሚፈልግ አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም ለመጪው የበጋ የስንዴ ምርት መዘጋጀት እንደሚገባ ነው ያመላከቱት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.