Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልልን የመጠጥ ውኃ እጥረት ለመፍታት እየተሠራ መሆኑ ተገለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልልን የመጠጥ ውኃ እጥረት ለመፍታት የአጭር፣ የረጅም እና መካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሯ በአቦቦ እና ጆር ወረዳዎች የተገነቡ ሦስት የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

ዛሬ ለምረቃ የበቁት ፕሮጀክቶችም የየአካባቢዎቹን ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውኃ ችግር እንደሚቀርፉ አስረድተዋል፡፡

የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኡጁሉ ኡዶል በበኩላቸው፥ ለሦስቱም ፕሮጀክቶች ከ74 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ከ16 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.