Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እንድታንሠራራ በትኩረት እንደሚሠራ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ በወቅታዊ ሀገራዊና መንግስት ትኩረት በሚያደርግባቸው የኢኮኖሚ እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫቸውም ሀገር በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ መንሠራራትን እንድታመጣ መንግስት በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

በጀት ዓመቱ የኢትዮጵያ መንሠራራት ዓመት ሲባል የምግብ ፍላጎትን ከማሟላት ጀምሮ ሁሉን አቀፍ መደላድልንም ማስፋት ላይ በመሥራት  መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ፖለቲካዊ አለመግባባቶችን በንግግር ለመፍታትም በሀገራዊ ምክክሩ የተጀመሩ ሥራዎች እውን እንዲሆኑ ይሠራል ነው ያሉት፡፡

ግብርናው ላይ የተጀመሩ የማሻሻያ ርብርቦች የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ መንሠራራት አስቻይ ተግባር ማሳያ እንደሆኑ አንስተዋል፡፡

በተለይም ግብርናውን ከተለምዷዊ አሠራሩ በተሻለ ዘመናዊ መንገድን በተከተለ ሁኔታ እየተከናወነ ባለው ተግባርም ዘርፉ በጥሩ ቁመናላይ የሚገኝ ሰብል እንዲኖር አስችሏል ብለዋል ሚኒስትሩ።

ይህንን ሰብል ያለብክነት ለመሰብሰብ ሁሉም አካል በርብርብ እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ያለፉት ዓመታት የበጋ መስኖ ስንዴ አበረታች መሆኑ ከሀገርምተሻግሮ አህጉራዊ ተቀባይነትን ያገኘ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ይህንን ተግባርም አጠናክሮ ለማስቀጠል ግብዓትን ተደራሽ ከማድረግ ጀምሮ ከፍተኛ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል የሌማት ትሩፋት ላይ ትኩረት አድርጎ በመሥራት ዜጎችን ከተረጅነት የማላቀቅ ሥራ እንደ ሀገር እየተሠራ መሆኑን ገልጸው፥ ይህም አበረታች ውጤት እያስመዘገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቱሪዝም ኢንዱስትሪውም ለሀገራዊ እድገት ያለውን የጎላ ሚና ወደ ተግባር በመቀየር የበኩሉን እንዲወጣ በፖሊሲ የታገዘ ስራ ማከናወን ተጀምሯል ነው ያሉት።

ለዚህ በማሳያነት እየተከናወኑ ያሉ የዘርፉን ገጽታ የሚያጎሉ የመዳረሻ ልማት ስራዎች ን ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ጉዳዮች ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ  እንደ አፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና ላሉት ተግባራት የሰጠችውን ትኩረትም ለአብነት አንስተዋል።

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.