Fana: At a Speed of Life!

የጨው ንግድ ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሞኖፖሊ አሠራር ተጋልጠው ከቆዩ ምርቶች መካከል ጨው አንዱ መሆኑን እና በዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

በሀገራችን የንግድ ስርዓት ውስጥ ከሚስተዋሉ ችግሮች አንዱ የንግድ ስርዓቱ ለውድድር የተመቸ ከመሆን ይልቅ ለሞኖፖሊ የተጋለጠ መሆኑ አንዱ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ለሞኖፖሊ አሠራር ተጋልጠው ከቆዩ ምርቶች መካከል የጨው ምርት አንዱ መሆኑን ገልጸው÷ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮችንና ሌሎች በግብይት ስርዓቱ ውስጥ የተስተዋሉ ማነቆዎችን ሊፈታ የሚያስችል የጨው ንግድ ግብይት መመሪያ ተከልሷል ብለዋል፡፡

ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋርም ፍሬያማ ውይይትና ግብዓት የማሰባሰብ ስራ ሠርተናል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.