Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ምክትል የህዝብ ደህንነት የተመራ ልዑክ የአዲስ አበባ ፖሊስን እየጎበኘ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ምክትል የህዝብ ደህንነት ሺ ያንጁን የተመራ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ፖሊስ የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

በጉብኝቱ በኢትዮጵያ የቻይና አምባደር ሺን ሀይን፣ የቤይጂንግ ከተማ ፖሊስ ኃላፊ ጃኦ ጃንሺን እንዲሁም የሪፐብሊኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እና የማኔጅመንት አባላቶች የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች የቆየ ትስስር በማንሳት እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡

የልዑኩ አባላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ቴክኖሎጂ መር የወንጀል መከላከል ስራዎች ላይ የጀመራቸው ስራዎችን በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.