Fana: At a Speed of Life!

ተጠባቂው የዛሬ ምሽት የቦክስ ፍልሚያ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ58 ዓመቱ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ጄክ ጆሴፍ ፖል ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ዛሬ ምሽት በአሜሪካ ቴክሳስ አርሊንግተን ይካሄዳል፡፡

ከዓመታት በፊት ቀጠሮ በተያዘለት ፍልሚያ የዓለም የቦክስ ባለታሪኩ ማይክ ታይሰን እና በ1997 ማይክ ታይሰን ልደቱን ካከበረለት ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ እና ዩቲዩበር ጄክ ጆሴፍ ፖል ጋር ይደረጋል፡፡

ከውድድሩ አስቀድሞው አንጋፋው ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን “ታይሰን አላረጀም አሁንም ጠንካራ ቡጢውን ተጋጣሚ ላይ ማሳረፍ የሚችል አቅም አለው” ሲል ስለእራሱ ተናግሯል፡፡

የቦክስ ፍልሚያውን የአሜሪካው ኔትፍሊክስ የስርጭት ማዕከል በቀጥታ የሚያስተላልፈው ሲሆን ከ280 ሚሊየን በላይ ሰዎች ይመለከቱታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምሽት 5 ሰዓት ላይ በቴክሳስ አርሊንግተን ኤቲ ኤንድ ቲ ስታዲየም የሚደረገውን ፍልሚያ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ስታዲየም ገብተው ይመለከቱታል ተብሎ እንደሚጠበቅ አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

የዓለማችን የምንጊዜም ታላቁ ቦክሰኛ ማይክል ጄራርድ ታይሰን በፈረንጆቹ ከ1985 እስከ 2005 ባደረጋቸው 56 ፕሮፌሽናል ግጥሚያዎች በ50ዎቹ ድል ሲቀዳጅ በ6ቱ ብቻ ተሸንፏል፡፡

“አይበገሬው”፣ “ብረቱ ማይክ” እና “አውሬው” በሚሉ ቅጽል ስሞች የሚጠራው ቡጢኛ ከድሎቹ ውስጥ 44ቱን ያስመዘገበው በዝረራ አሸንፎ ነው፡፡

ከማይክ ታይሰን ጋር የሚፋለመው ወጣቱ ቦክሰኛ ጆሴፍ ፖል 10 ፕሮፌሽናል ውድድሮችን አድርጎ ዘጠኙን ሲያሸንፍ በአንዱ ብቻ ተሸንፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.