ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በፖሊስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መሃዲ ከሀገሪቱ ፖሊስ ሃላፊ ጄነራል አተም ማሮል ቢያር ኩክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት ፖሊስ ተቋማት መካከል ባለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ትብብር ዙሪያ መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቅርቡ ለደቡብ ሱዳን ፖሊስ ኦፊሰሮች በሰጠችው የስልጠና እድል ዙሪያና በሌሎች የትብብር ዘርፎች መወያየታቸውንም የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከርና የሀገራቱን ሕዝቦች ብሎም የቀጣናውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ሀገራቱ በፖሊስ ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተጠቁሟል፡፡