Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ የመወሰን አቅምን ከተጠያቂነት ጋር አጣምሮ የሚሰጥ ነው – አቶ አሕመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመንግስት የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ውይይቱን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ÷ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ለተቋማትና የሥራ ሃላፊዎች የመወሰን አቅም ከተጠያቂነት ጋር አጣምሮ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ግዢ የሚፈጽሙ በመሆናቸው ከዚህ ቀደም ሲያነሷቸው የነበሩ የግዢ ችግሮችን ለመፍታት እንዲየግዝ ተደረጎ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

ረቂቅ መመሪያው ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው፣ ተገቢ ቁጥጥር ለማስፈንና በማዕከላዊነት ለማስተባበር የሚያስችል ሆኖ መዘጋጀቱንም አስረድተዋል፡፡

በውይይቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመሪያው ይበልጥ እንዲዳብር የበኩላቸውን የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

መመሪያው በቅርቡ የጸደቀውን የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መሠረት አድርጎ መዘጋጀቱንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.