በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሕዝባዊ ሰልፎች ተካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላምን ለማፅናት ያለመ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።
ሕዝባዊ ስልፉ በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ቄለም ወለጋ እና የአርሲ ዞኖች እየተደረገ ሲሆን፤ በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተለያዩ ሕብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።
የሰልፉ ተሳታፊዎች ‘ሰላምን ለማጽናት የበኩላችንን እንወጣለን’፣ ‘በሰላም እጦት ምክንያት የህዝቡ ስቃይ ሊቆም ይገባል’፣ ‘ወደ ሰላም መመለስ መሰልጠን ነው’ የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን ማስተላለፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።