Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ባይደን ትራምፕን በዋይት ሃውስ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዋይት ሃውስ ለዶናልድ ትራምፕ አቀባበል አድርገዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ፕሬዚዳንት ባይደን “ዶናልድ ትራምፕ እንኳን ተመልሰው መጡ” በማለት የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን በመግለጽ ነው አቀባበል ያደረጉላቸው፡፡

በቅርቡ ከኃላፊነት የሚሰናበቱት ጆባይደን እና ተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ በሥልጣን ሽግግሩ ላይ ስለሚኖሩ ሁኔታዎች እንደሚመክሩም ይጠበቃል ተብሏል፡፡

የስልጣን ሽግግሩም ሠላማዊ እንደሚሆን በሁለቱም ወገን መገለጹን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የሩፐብሊካኑ ትራምፕ ሰሞኑን ካማላ ሃሪስን በሰፊ ልዩነት በማሸነፍ ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት መመረጣቸው ይታወሳል፡፡

ትራምፕ ከፕሬዚዳንት ባይደን በፊት ለአንድ ተርም (አራት ዓመታት) አሜሪካን በፕሬዚዳንትነት መምራታቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.