የኢትዮጵያ ልዑክ ከአየር ንብረት ኢንቨስትመንት ድጋፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ በሚገኘው የኮፕ 29 ጉባዔ እየተሳተፈ ያለው የኢትዮጵያ ልዑክ ከአየር ንብረት ኢንቨስትመንት ድጋፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ ታሪዬ ግባድጌሲን ጋር ተወያየ፡፡
ከጉባዔው ጎን ለጎን የተደረገው ይህ ውይይት የደን ልማት ላይ ያተኮረ መሆኑን እና ስኬታማ እንደነበር ልዑኩ መግለጹን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚሁ ወቅትም ታሪዬ ግባዴጌሲን ኢትዮጵያ የአየር ንረት ለውጥን ለመዋጋት እያሳየች ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡