Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ፕሮጀክቶች የዓለም ማህበረሰብ ድጋፍ ማድረግ አለበት – ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለመከላከል ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው ለምትገኘውና መሰል ፕሮጀክቶች ዓለምአቀፉ ማኀበረሰብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ29) ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን ጨምሮ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ ጉዞ እና የምታደርጋቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስረድተዋል።

በተጨማሪም እንዲህ ዓይነት መሰል ጥረቶች እንዲጎለብቱ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.