Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያውን ዕድል አሟጦ ለመጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪቱን ከማስፋትና ከማዘመን በሻገር ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያው ያለውን ዕድል አሟጦ ለመጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በ5ኛው ሀገር አቀፍ ብሔራዊ የሥራ ኤክስፖ አፈፃፀምና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ ቀጣሪ ድርጅቶችንና የተቋማትን ውጤታማነት የሚያልቁ ሥራ ፈላጊዎችን የማገናኘቱን ሥራ አጠናክሮ ከማስቀጠል ባሻገር የሥራ ፈጠራ ስነ-ምህዳሩን ማስፋት የሚያስችሉ ጉዳዮችን በዝርዝር ተነስተዋል፡፡

በዚህም ቀጣሪ ድርጅቶችንና የተቋማትን ውጤታማነት የሚያልቁ ሥራ ፈላጊዎችን የማገናኘቱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

የሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪቱን ከማስፋትና ከማዘመን በሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ የርቀት የሥራ መስክን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያሉ እድሎችን አሟጦ ለመጠቀም እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡

በዚህም የግሉ ዘርፍ ሚናውን እንዲወጣ የማስቻል፣ ማነቆዎችን በመፍታት እና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መገለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.