ሩድ ቫኒስትሮይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በይፋ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሆላንዳዊው የቀድሞ የእግር ኳስ ኮከብ ሩድ ቫን ኒስትሮይ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር በይፋ ተለያይቷል፡፡
የ48 ዓመቱ የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ ኮከብ በሁለት ዓመት የኮንትራት ውል የማንቼስተር ዩናይትድ ምክትል አሰልጣኝ ለመሆን መስማማቱ ይታወሳል፡፡
የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን ስንብት ተከትሎም ቫን ኒስትሮይ ማንቼስተር ዩናይትድን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሲመራ የቆየ ሲሆን÷ሶስት ጨዋታዎችንም ማሸነፍ ችሏል፡፡
ይሁን እንጅ አዲስ የማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ በመሆኑ የተሾሙት ሩበን አሞሪም በራሳቸው የአሰልጣኝ ቡድን (ኮቺንግ ስታፍ )አባላት ቡድኑን ለማዋቀር መፈለጋቸውን ተከትሎ ቫን ኒስትሮይ በይፋ ከክለቡ ጋር ተለያይቷል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ የኮከቡን ስንበት ተከትሎ ባወጣው መግለጫ÷ ሩድ ቫን ኒስትሮይ ሁልጊዜም የማንቼሰትር ዩናይተድ ባለታሪክ ሆኖ ይቀጥላል ብሏል፡፡
በአምስት የውድድር ወራት ውስጥ ላበረከተው አስተዋፅኦም ክለቡ ምስጋና አቅርቧል፡፡