በድሬዳዋ የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን በላቀ ደረጃ ለማሳካት እንደሚሰራ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ የለውጥ ሥራዎችን በላቀ ደረጃ ዳር ለማድረስ ርብርቡ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር አስታወቁ።
በድሬዳዋ “የሃሳብ ልዕልና፤ ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያስቃኝ የፎቶ አውደ ርዕይ ተከፍቷል።
በዚሁ ጊዜ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር÷ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በድሬዳዋ ባለፉት አምስት ዓመታት ታላላቅ ስኬቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በዚህም በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶች ብልፅግናን ለማረጋገጥ መሠረታዊ ምሰሶዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም በአስተዳደሩ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ የለውጥ ሥራዎችን በላቀ ደረጃ ዳር ለማድረስ ርብርቡ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የፎቶ አውደ ርዕዩም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ዘርፎች የተገኙ ታላላቅ ድሎችን ለማስቃኘትና ለተሻለ ለውጥ ለመነሳሳት እንደሆነ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡