ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ወደ ኪሊማንጃሮ በረራ ሊያደርግ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ትልቁ ተራራ መገኛ ወደ ሆነው ኪሊማንጃሮ በኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን በራራ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ÷የአፍሪካ ትልቁ ተራራ መገኛ ወደሆነው ኪሊማንጃሮ በዛሬው ዕለት በአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ከፍ ብለን ለመብረር ዝግጅታችንን አጠናቅቀናል ብሏል።