Fana: At a Speed of Life!

የሠላምና ፀጥታው ዘርፍ ልዩ ክብር የሚሰጠው ሙያ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)የሠላምና ፀጥታው ዘርፍ ልዩ ክብር የሚሰጠው ሙያ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም ለተልዕኮው መሳካት ጉልህ ሚና ለነበራቸው አካላት የዕውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

በመርሐግብሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ የፀጥታው ዘርፍ አስቸጋሪ ፈተናዎችን ተቋቁሞ እዚህ በመድረሱ ክብር ይገባዋል ብለዋል።

ከለውጡ ወዲህ መዲናዋን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ በፀረ ሠላም ኃይሎች በትኩረት ሲሰራ እንደነበር ያስታወሱት ከንቲባዋ ያንን አስቸጋሪ ወቅት በብልሀት አልፋችሁ ሠላምን በማፅናታችሁ አድናቆት ይገባችኋል ብለዋል፡፡

“ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በቅርበት በመስራት ከተማችን ፍጹም ሰላማዊ እንድትሆን እና ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ እየሰራችሁ ለምትገኙ የጸጥት አካላት በሙሉ ላደረጋችሁት አስተዋፅዖ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ” ብለዋል።

በቀጣይም ይህን ስኬት በላቀ ደረጃ የማስቀጠሉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ከንቲባዋ የሠራዊቱን የኑሮ ደረጃ ለማሻልም ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በወንድሙ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.