የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አጀንዳውን ለምክክር ኮሚሽኑ አስረከበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተወካዮች የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከበ፡፡
በክልሉ ሲካሄድ የነበረው አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር መድረክ ተጠናቋል፡፡
አጀንዳውን የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ሥላሴ፣ ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ እና ኮሚሽነር ዘገዬ አስፋው ከክልሉ ተወካዮች ተረክበዋል።
ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር÷ ባለፉት ሰባት ቀናት በክልሉ የተካሄደው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ውጤታማ ሆኖ መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
አጀንዳ የማሰባሰብ መድረኩ ጥልቅ ውይይቶች እና መግባባቶች የተስተዋሉበት ሀሳቦች በነጻነት ተንሸራሽረው አጀንዳዎች የተለዩበት እንደነበርም ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ ኮሚሽኑ በክልሉ የነበረው አጀንዳ የማሰባሰብ ምዕራፍ የተሳካ እንደነበር ጠቅሰው÷ በአጀንዳ የማሰባሰብ ሂደቱ ወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች የተነሱበት እንደነበር ገልጸዋል።
በይስማው አደራው