ከረሃብ ነፃ ዓለም ጉባኤ ላይ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በተካሄደው ከረሃብ ነፃ ዓለም ጉባኤ ላይ ተሳታፊ የነበሩ መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመሪዎቹ አሸኛኘት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የኢንዲስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ትብብር የተዘጋጀው ከረሀብ ነፃ ዓለም ጉባዔ ከጥቅምት 26 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄዱ ይታወቃል።