የህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር የባህልና ስፖርት ዘርፍ አቅምን መጠቀም ይገባል-ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከር የባህልና ስፖርት ዘርፍ አቅምን መጠቀም ይገባል ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ተናገሩ፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ ክንውን ላይ በአዲስ አበባ እየተወያየ ነው፡፡
በውይይቱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ ÷የባህልና ስፖርት ዘርፍ ለህዝቦች አብሮነትና ትስስር እንዲሁም ለሀገር ግንባታ ሂደት አስተዋፅኦ እንዲያደርግ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት በመስራት የባህልና ስፖርት ዘርፍ ጎልቶ እንዲወጣ ሚናቸው ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ ማጠናቀቂያ የውይይቱ ተሳታፊዎች እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የስፖርት መሠረተ ልማቶች፣ የኪነ-ጥበብና ሥነ-ጥበብ ስራዎችንና ማዕከላትን እንደሚጎበኙ ተጠቁሟል፡፡
በሻምበል ምህረት