Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት ጉባዔ ለማስተናገድ ያለውን ዝግጁነት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት (ኤአይኦ) ጉባዔ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት (ኤአይኦ) ሊቀመንበር ፓቲ ካርዋህ ማርቲን እና ዋና ፀሃፊ ቱካማዚና ዣን ባፕቲስትን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይቱም ወቅት በቀጣይ የሚካሄደውን 51ኛው የኤአይኦ ጉባዔ ለማስተናገድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያለውን ዝግጁነት ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ጉባዔው ለማካሄድና የእንግዳ ተቀባይነት ባህሏን ለማሳየት እንዲሁም የአህጉሪቱን የኢንሹራንስ ዘርፍ ለማስፋፋት ዝግጁ መሆኗም ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.