Fana: At a Speed of Life!

ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንደሚያደርጉ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትጆ ባይደን ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንደሚያድጉ ቃል ገብተዋል፡፡

ጆ ባይደን በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዴሞክራት ፓርቲ በሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ መሸነፉን ተከትሎ ለሀገሪቱ ሕዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም፥ የምርጫውን ውጤት እንደሚቀበሉ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡

ጆ ባይደን በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ዴሞክራትፓርቲን በመወከል ብርቱ ፉክክር ላደረጉት ካማላ ሃሪስ አድናቆታቸውን ችረዋል፡፡

በተመሳሳይ ለተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዚዳንቱ÷የሥራ ዘመናቸው ስኬታማ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

በአሜሪካ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ለመግባት 74 ቀናትን የሚጠብቁ ሲሆን ÷ እስከዚያ ድረስም ጆ ባይደን በስልጣን ላይ የሚቆዩ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል ካማላ ሃሪስ ሽንፈታቸውን ተቀብለው ለተመራጩ ፕሬዚዳንት መልካም ምኞታቸውን የገለጹ ሲሆን÷ ትራምፕ በበኩላቸው ከፍተኛ ሹመቶችን ለመስጠት ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡

የትራምፕ በዓለ ሲመት በፈረንጆቹ ጥር 20 መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.