ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‹‹የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደህና መጡ›› ሲሉ ገልጸዋል።