የ2024 አፍሪካን እናወድስ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024 አፍሪካን እናወድስ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ የአፍሪካ የንጉሳውያን ስርአት መሪዎች፣ የቢዝነስ አንቀሳቃሾች፣ የፈጠራ ሰዎች እንዲሁም የጥበብና ፋሽን ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
በዚህ ሁነት ላይ አፍሪካዊያን ባለሙያዎች ምርቶቻቸውን ይዘው የቀረቡበትና ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎችንም የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ህንፃ ውስጥ ተከፍቷል።
የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአፍሪካ ቱሪዝም ማዕከሏ አዲስ አበባ በምትታወቅበት ድምቀት እንግዶቿን እያስተናገደች ትገኛለች ብለዋል።
ሁነቱ ኢትዮጵያ ይበልጥ የምትደምቅበት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡