Fana: At a Speed of Life!

ከረሃብ ነጻ ዓለምን ለመፍጠር ኢንቨስትመንትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ማተኮር ይገባል – ገርድ ሙለር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከረሃብ ነጻ ዓለምን ለመፍጠር ኢንቨስትመንትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ገለጹ፡፡

“ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት” በሚል መሪ ሃሳብ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ከረሃብ ነጻ ዓለም ኮንፈረንስ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በመድረኩ እንደተናገሩት÷ ኢትዮጵያ ረሃብ እንዲያበቃ አርሶ አደሮች እና ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ የሥራ ዕድል እየፈጠረች ነው፡፡

የኢትዮጵያን አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ቁልፍ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመው÷ ዘላቂ የምግብ ዋስትና ለማረጋጋጥ አግሮ ኢንዱስትሪ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የዓለም ዓቀፉ ማሕበረሰብ ሊደግፈው እንደሚገባ ጠቅሰው ጥሪ ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡

ገርድ ሙለር በበኩላቸው÷ ከረሃብ ነጻ ዓለምን ለመፍጠር ኢንቨስትመንት እና የሥራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በተለይም በአፍሪካ የግብርናን ዘርፍ ቴክኖሎጂ መር በሆነ መልኩ ማሳደግ እንደሚጠበቅም ነው ያስገነዘቡት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.