በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሲካሄድ የቆየው የማህበረሰብ ወኪሎች የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የማህበረሰብ ወኪሎቹ ከጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የወከሉት ማህበረሰብ አጀንዳዎች በውይይት ሲያደራጁ ቆይተዋል፡፡
በውይይት ያደራጁትን አጀንዳ በአደራ ተረክበው ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚመካከሩ ወኪሎችንም መምረጣቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
የክልሉ የባለድርሻ አካላት ምክክርም ቀጥሎ ባሉ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን÷ በመድረኩ ከማህበረሰብ ወኪሎች የተመረጡ ተሳታፊዎችን ጨምሮ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ የልዩ ልዩ ማህበራትና ተቋማት ወኪሎች የሚሳተፉ ይሆናል፡፡