Fana: At a Speed of Life!

ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ለአየር መንገዱ ከፍተኛ አቅም የሚጨምር ነው – አቶ መስፍን ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን መዳረሻዎቹን እያስፋፋ ለሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ አቅም የሚጨምር ነው ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የአየር መንገዱ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ዛሬ አዲስ አበባ ሲገባ የአቀባበል መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሐ-ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ መስፍን ጣሰው÷ አውሮፕላኑ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ታሪካዊ እምርታን ያመጣል ብለዋል።

በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ መዳረሻዎቹን እያስፋፋ ለሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ አቅም እንደሚጨምር ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዋና አዛዥና የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው÷ ዛሬ የተቀበልነው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን የአየር መንገዱን በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱንና ደረጃውን ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
አየር መንገዱ አፍሪካን በማስተሳሰር ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው ጠቅሰው÷ ኢትዮጵያ ለምታደርገው የወጪና የገቢ ንግድ መሳለጥ ሁነኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

 

“ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አውሮፕላኑ 400 መቀመጫዎች አሉት።

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.