Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወባ ሥርጭት ሊጨምር ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ ታኅሣስ ወር 2017 ዓ.ም ድረስ የወባ በሽታ ሥርጭት ሊጨምር ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡

የወባ በሽታን ሥርጭትን አስመልክቶ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና በክልሉ በየደረጃ ከሚገኙ አመራሮች ጋር በቡታጅራ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በዚሁ ወቅት በአግባቡ የወባ በሽታን የመከላከልና መቆጣጠር ሥራ ካልተከናወነ ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን ያነሱት የቢሮው ኃላፊ ሳሙኤል ዳርጌ÷ ችግሩን ለመቆጣጠር የሕዝቡን ግንዛቤ ማሳደግ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ለዚህም በቀጣይ ወራት በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አካላት ከመገናኛ ብዙኃን ጋር በመቀናጀት ሕዝቡ ጉዳት እንዳይደርስበት ማድረግ አለባቸው ነው ያሉት፡፡

ከአጎበር አጠቃቀም ጀምሮ የሚታዩ ክፍተቶችን ማረምና ትክክለኛውን መረጃ ሕዝቡ እንዲያገኝ ማድረግ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡

80 በመቶ የክልሉ አካባቢ ለወባ መራቢያ ምቹ ስለሆነ የሥርጭት መጠኑ መጨመሩን ጠቅሰው÷ ለአብነትም በሩብ ዓመቱ ከተመረመሩ 396 ሺህ 520 ሰዎች መካከል 99 ሺህ 901 ያህሉ የወባ በሽታ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.