በደብረ ማርቆስ ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ማርቆስ ከተማ በወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ዙሪያ የሚመክር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
ኮንፈረንሱ “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመድረኩ በከተማ አስተዳደሩ ከአራቱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡