የሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተሳታፊዎች አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ እና የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተሳታፊዎች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
የሩሲያ እና የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተሳታፊዎችም ወደከተማዋ እየገቡ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ መሀመድ ቢን ዘይድ ዩኒቨርሲቲ ፎር ሂዩማኒቲ ቻንስለር ዶ/ር ኸሊፋ አል ደህሪ የሚመራ የሀገሪቱ ልዑክ፣ የሳዑዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ አሜሪካና ሊባኖስ ተወካዮች በሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በተመሳሳይ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ መሀመድ ቢን ዘይድ ዩኒቨርሲቲ ፎር ሂዩማኒቲ ቻንስለር ዶ/ር ኸሊፋ አል ደህሪ የሚመራ የሀገሪቱ ልዑክ፣ የሳዑዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ አሜሪካና ሊባኖስ ተወካዮች በሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) አቀባበል ተደርጎላቸዋል።