ሩሲያ ሁለት ተጨማሪ የዩክሬን መንደሮችን ተቆጣጠረች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ሁለት ተጨማሪ የዩክሬን መንደሮችን እንደተቆጣጠረች የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሩሲያ ወታደሮች በካርኪቭ ግዛት ፔርሾትራቭኒቭ እና በዶኔስክ ግዛት ኩራክሂቭካ የተሰኙ የዩክሬን መንደሮችን ነው የተቆጣጠሩት፡፡
በአካባቢው ሲደረግ በቆየው ፍልሚያ በርካታ የዩክሬን ጦር መሳሪያዎች መማረካቸውና መውደማቸውም ተገልጿል፡፡
በዚህም በርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ድሮኖች፣ ታንኮች፣ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችና የሮኬት ማስወንጨፊያዎች መውደማቸው ተጠቁሟል፡፡
በአንጻሩ በጉዳዩ ላይ ከዩክሬን መንግስት በኩል የተባለ ነገር አለመኖሩን
የቲ አር ቲ ዘገባ አመልክቷል፡፡