276 ኢትዮጵያውያን ከኬንያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ በእስር ቤት የነበሩ 276 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ በሕገ-ወጥ ደላሎች ተታልለው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ሲሞክሩ በኬንያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በ11 የተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡
ተመላሾቹ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባደረገው ጥረት ከእስር ቤት ተለቀው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የኤባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡