Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ የኮሪደር ልማት ስራ ለመሳተፍ መዘጋጀቱን የሞሀ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ.ማ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ለማልማት መዘጋጀቱን የሞሀ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል፡፡

የክሲዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ሙሄ÷ድርጅቱ በኮሪደር ልማቱ በመሳተፍ በከተማዋ ውበት ላይ ሌላ ውበት ለመጨመር ይሰራል ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ ብሩክ ሰለሞን በበኩላቸው÷ ፋብሪካዎች ከተማዋን በማልማት ሀላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡

የሞሀ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር በቀዳሚነት የኮሪደር ልማት ስራ መጀመሩንም ጠቅሰዋል፡፡

ከኮሪደር ልማት ባሻገር ለስራ እድል ፈጠራ የሚሆን 30 ሼዶችን በማዘጋጀት ስራ አጥ ዜጎችን ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት መጠናቀቁን የገለጹት ደግሞ የሐዋሳ ሚሊኒየም ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ስጦታው ታደሰ ናቸው፡፡

ሞሀ ባዘጋጀው ”ጣመኝ ድገመኝ” የሽልማት መርሐ ግብር የሁለተኛዋ መኪና ባለእድለኛ የሆነው ወጣቱ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ ሽልማቱን የተረከበ ሲሆን÷በቀጣይም ቀሪ ሰባት ተሽከርካሪዎች ለሽልማት መዘጋጀታቸው ተመላክቷል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው እና ጥላሁን ይልማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.