26ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 26ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤው “የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ እምርታ ለተፋጠነ የዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በጉባኤው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የጤናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በሳሙኤል ወርቃየሁ