Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን አፅናኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በክልሉ ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በስፍራው በመገኘት አፅናንተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የመሬት መንሸራተት አደጋ በተደጋጋሚ እየተከሰተ እንደሆነ ገልጸው፤ አደጋው የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል በየደረጃው ያለው የመንግስት መዋቅር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወጎኖችም መፅናናትን ተመኝተዋል።

በወረዳው ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ስጋት ያለባቸው አካባቢዎችን በመለየት 1 ሺህ 254 ቤተሰቦችን በጊዜያዊ መጠለያ፣ በሀይማኖት ተቋማት፣ በቀበሌ ቤቶችና በአርሶአደር ማሰልጠኛ እንዲቆዩ የማድረግ ስራ መሰራቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

ከአደጋዉ በኋላ ተጎጂዎችን የማስወጣት ስራ መሰራቱን ገልጸው፤ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ተጎጂዎችን የመደገፍ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

በክልሉ ዎላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጉዳት ከትናንት በስቲያ የሰባት ወገኖች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.