Fana: At a Speed of Life!

በከተማ ግብርና ምርታማነትን በመጨመር ዜጎች እንዲጠቀሙ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማ ግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሀገሪቱ በሁሉም ከተሞች እየተሠራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ሶፍያ ካሳ (ዶ/ር) በሲዳማ ክልል የከተማ ግብርና እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

በሐዋሳ ከተማ እየተተገበረ ያለው የከተማ ግብርና ሥራ አበረታች ቢሆንም÷ ከተማው ካለው ሰፊ ቦታና አቅም አንጻር ገና ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅበት በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡

የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ መምሩ ሞኬ÷ በእንስሳት ልማት፣ በዶሮ እርባታና በጓሮ አትክልት እንዲሁም በሰብል ልማት የበጋ መስኖዎችንም ጭምር በመጠቀም በስፋት ለማልማት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከተጎበኙት መካከል በባለሃብቶች የለሙ ሰፋፊ እርሻዎችና የእንስሳት እርባታዎች፣ በግለሰቦች መኖሪያ ቤት አነስተኛ ቦታዎች ላይ የተከናወኑ የእንስሳት፣ የዶሮና የጓሮ አትክልት ልማቶች እና ሌሎችም እንደሚገኙበት የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.