Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲው ከ6 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ ግንባታ እያከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ6 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ ግንባታቸው እየተከናወኑ ከሚገኙ 28 ፕሮጀክቶች መካከል አራቱ ተጠናቅቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

እንዲሁም 24 የግንባታ ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ በዩኒቨርሲቲው የግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ መሐመድ አዳነ (ኢ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የዋጋ ንረት፣ የፋይናንስ እጥረት፣ የሲሚንቶና የብረት አቅርቦት ማነስ እንዲሁም የዋጋ ማሻሻያ ክፍያ መዘግየት ግንባታዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል በ2017 የበጀት ዓመት የመረጃ ማዕከል፣ የቆሻሻ ውኃ ማከሚያ፣ የሕጻናት ማቆያ፣ የመጠጥ ውኃ ዝርጋታ እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን መሰረተ-ልማቶችን ለመገንባታ ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በከድር መሐመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.