Fana: At a Speed of Life!

ኢንዱስትሪዎች ከውጪ ያሉ የገበያ ዕድሎችን ለመጠቀም መስራት እንዳለባቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሀገር ውጪ ያሉ የገበያ ዕድሎችን ለመጠቀም በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ መስራት እንዳለባቸው የኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር  መላኩ አለበል ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና አመራሮች ጋር በወጪ ምርቶች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በዚህ ወቅትም አቶ መላኩ÷ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከውጭ ያሉ የገበያ ዕድሎችን ለመጠቀም በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የመግዛት አቅም ያላቸውን የውጭ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመጋበዝ ሀገሪቱ  ያላትን ምቹ የገበያ ሁኔታ እንዲገነዘቡ የማድረግ ስራ እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

የውጪ ገዥዎችን ለመሳብ  በሚደረገው ጥረት መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውንም  የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.