Fana: At a Speed of Life!

ኢንዱስትሪው ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ እንዲያበረክት መሥራት ይገባል – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማይስ ኢንዱስትሪ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ የሚያበረክት የዳበረ የሁነት ኢንዱስትሪ እንዲሆን መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ከሁነት አዘጋጆች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም የትብብር እድሎች፣ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶች እና ኢትዮጵያን ዋና የማይስ መዳረሻ ለማድረግ በሚበጁ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የማይስ ኢንዱስትሪ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ የሚያበረክት የዳበረ የሁነት ኢንዱስትሪ እንዲሆን መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነትም ሚኒስትሯ በአጽንኦት ገልፀዋል።

ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያን ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ መገንባታ ዋና ሥራው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ለዚህም የዘርፉን እድገት የሚያበረታቱ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት እና ወደ ተግባር እንዲገቡ በማድረግ ለመደገፍ መንግሥት ቁርጠኛ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የድርጅቶቹ ተወካዮች በበኩላቸው በኢንዱስትሪው ፍላጎቶች ላይ ያላቸው ግንዛቤ በማካፈል በአፍሪካም ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ከመውጣት አንጻር የሚነሱ ተግዳሮቶችን አንስተዋል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያም መደበኛ የግንኙነት አግባብ በመፍጠር አጋርነትን ለማጎልበት እንደሚያስፈለግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.