በስፔን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ51 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ቫሌንሺያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በትንሹ የ51 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
የአካባቢው ገዢ ካርሎስ ማዞን÷ የተከሰተውን አደጋ ተከትሎ 1ሺህ ወታደሮችና በርካታ የነፍስ አድን ሰራተኞች በስፍራው መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡
በአደጋው እስካሁን የ51 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ጠቁመው÷የሟቶች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል አመልክተዋል፡፡
በአካባቢው በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያም የባቡርና የአየር ትራንስፖርት መቋረጡን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡