እስራኤል በጋዛ የእርዳታ ድርጅቶች ላይ የጣለቸው ክልከላ አሳሳቢ መሆኑን ተመድ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል የእርዳታ ድርጅቶች ለጋዛ ሕዝብ እርዳታ እንዳያቀርቡ የጣለችው ክልከላ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ይበልጥ አስከፊ እንዳደገረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡
የተመድ የሰላም ማስከበር ሃላፊ ጂያን ፒር ላክሮክስ እንዳሉት÷ለጋዛ ነዋሪዎች አብዛኛውን የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡት የእርዳታ ድርጅቶች በመሆናቸው የእስራኤል ክልከላ ሁኔታውን አስከፊ አድርጎታል፡፡
በአካባቢው የሰብዓዊ እርዳታ እንቅስቃሴ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው÷ የድርጅቶቹ ክልከላ በጋዛ ያሉ ነዋሪዎች በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡
እስራኤል ክልከላውን በፓርላማዋ ለማጸደቅ የምታደርገው ጥረት ተግባራዊ እንዳይሆን ጫና ማድረግ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡
በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 ቀን 2023 በተጀመረው የእስራኤል ሃማስ ጦርነት እስካሁን 43 ሺህ በላይ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የፊልስጤም ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በትናንትናው ዕለት ብቻ እስራኤል በሰሜን ጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከ93 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡