ጤና ሚኒስቴር 100 ‘ሀርድ ቶፕ’ እና 160 ‘ፒካፕ’ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 572 ሞተርሳይክሎችን ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር 100 ‘ሀርድ ቶፕ’ና 160 ‘ፒካፕ’ ተሽከርካሪዎችን ፣ 572 ሞተር ሳይክሎችን፣ 2 ሺህ 700 ኮምፒውተሮችን ጨምሮ ሞባይል ክሊኒኮችን ለተጠሪ ተቋማቱ፣ ለክልልና ከተማ አሥተዳደር ጤና ቢሮዎች እና ለሆስፒታሎች ድጋፍ አደረገ፡፡
የተደረገው ድጋፍ የጤና አገልግሎቱን የተሳለጠ ለማድረግ እና የጤና ሥርዓቱን ለማዘመን እንደሚያግዝ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል፡፡
የጤና ተቋማት አገልግሎት የተሳለጠ እና ተደራሽ እንዲሆን አሠራራቸውን ዲጅታላይዝ ለማድረግ፣ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂና በግብዓት በበቂ ሁኔታ የማደራጀት ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን