Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ19ኛው የኮሜሳ የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እየተሳተፈችበት የያለው የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) 19ኛው የሚኒስትሮች ጉባዔ በቡሩንዲ ቡጁምቡራ እየተካሄድ ነው፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ሕብርትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ የተመራ ልዑክ በጉባዔው እየተሳተፈ ነው፡፡

ጉባዔው የኮሜሳ የሰላምና የጸጥታ ፕሮግራሞች አፈጻጸም ያሉበትን ደረጃ መገምገሙን በካምፓላ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚሁ መሠረትም በሊቢያ፣ ሱዳን፣ ምሥራቃዊ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ሶማሊያ ስላለው ወቅታ ጸጥታ ሁኔታ መምከሩን ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ስለ አየር ንብረት ለውጥ እና በቀጣናው የሚካሄዱ ምርጫዎችን በተመለከተ በጉባዔው ምክክር መደረጉ ተነስቷል፡፡

በተጨማሪም ጉባዔው ነገ በሚካሄደው 23ኛው የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.