Fana: At a Speed of Life!

ድህነትን ለማሸነፍ አማራጮቻችንን በአግባቡ መጠቀም ይገባል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ድህነትን ለማሸነፍ ያሉንን የልማት አማራጮች ሁሉ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ሲሉ ኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አስገነዘቡ፡፡

በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የክልሉ መንግሥትና የፓርቲ የሦስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናቅቋል፡፡

በግምገማው ላይ ባለፉት ሦስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በጥንካሬ እና በክፍተት የታዩ ጉዳዮች ተለይተው ውይይት መደረጉን በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚሁ ወቅት አቶ ሽመልስ ባደረጉት ንግግር÷ የብልጽግናን ዐቢይ የትኩረት መስኮች ለማሳካት ያሉንን የተለያዩ የልማት አማራጮች መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡

ለዚህም በዕውቀት እና ክኅሎት መር አመራር ሰጭነት በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት፡፡

ባለፉት ሦስት ወራት በክልሉ በተተገበረው አዲስ የቀበሌ አደረጃጀት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች መከናወናቸውንም አንስተዋል፡፡

በቀጣይም የተያዙ ዕቅዶች እንዲሳኩ በየደረጃው የሚገኙ አካላት በልዩ ትኩረት መሥራት ይገባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.