Fana: At a Speed of Life!

ቼልሲ ሲያሸንፍ ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ፣ ክሪስታል ፓላስ እና ዌስትሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ቼልሲ ከኒውካስል ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ግቦቹን ጃክሰን እና ፓልመር አስቆጥረዋል፡፡

የኒውካስልን ብቸኛ ግብ ደግሞ ኢሳቅ አስቆጥሯል፡፡

ክሪስታልፓላስ ቶተንሃምን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ግቧን ማቴታ አስቆጥሯል፡፡

እንዲሁም ዌስትሃም እና ማንቼስተር ዩናይትድ ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

የዌስትሃምን ግብ ሰመርቪል እና ቦውን ሲያስቆጥሩ የማንቼስተር ዩናይትድን ብቸኛ ግብ ደግሞ ካስሜሮ ከመረብ አገናኝቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.